Notice በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

06th July, 2024

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እንዲካሄድ በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ።

(ሰኔ 25/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በየደረጃው ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና መምሪያ ኃላፊዎች፣ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም ከደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዘዳንቶች ጋር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በተዘጋጀ የጸጥታ እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሩ አመራሮችና አባላት እያደረጉ ለሚገኘው የማይቋርጥ ድጋፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበው ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ቁጥር በመጨመሩ ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲሰጥ ከጸጥታ አካላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ስጋትም ሆነ ሌሎች የፈተናውን ሂደት ከሚያውኩ ተግባራት ተጋላጭነት በጸዳ መልኩ እንዲካሄድ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስም ሆነ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሩ አባላት በፈተናው ሂደት ተገቢውን  የጥበቃ፣ፍተሻ እና እጀባ ተግባራትን በማከናወን ፈተናው ከማንኛውም የጸጥታ ስጋት ነጻ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጌቱ አርጋው አስታውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! 

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

.

Copyright © All rights reserved.