Notice ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ኦን ላይን ተፈታኞች የሙከራ ፈተና ተሰጠ

ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ኦን ላይን ተፈታኞች የሙከራ ፈተና ተሰጠ

06th July, 2024

ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ኦን ላይን ተፈታኞች በዛሬው እለት የሙከራ ፈተና ተሰጠ፡፡

(ሰኔ 25/2016 ዓ.ም) የሙከራ ፈተናው አብርሖት ቤተ መጽሀፍትን ጨምሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የኦን ላይን መፈተኛ ጣቢያዎች የተሰጠ ሲሆን የሙከራ ፈተናው በዋናነት የፈተና ጣቢያዎቹን ዝግጁነት በማረጋገጥ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም እንከን መውሰድ እንዲችሉ የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ለመገምገም ታስቦ መሰጠቱን ከመርሀ ግብሩ አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ኦን ላይን  ፈተናን በስኬት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኢትዮ ቴልኮም እና ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  ጋር በጋራ በመሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  አመራሮች ጋር በመሆን  የሙከራ ፈተና ሂደቱን ለመከታተል በአብርሖት ቤተ መጽሀፍ በሚገኘው የፈተና ጣቢያ በተገኙበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በሙከራው የፈተና ሂደት የኮመፒወተሮች ዝግጁ መሆን የኢንተርኔት አገልግሎቱ አስተማማኝነት እንዲሁም እንዲሁም በየፈተና ጣቢያዎቹ ጄኔሬተሮችና ሌሎች ለኦን ላይን ፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች  መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ከመገለጹ ባሻገር ልምምዱ ተፈታኝ ተማሪዎቹን ለፈተናው በአግባቡ እንዲዘጋጁ ያስቻለ ተግባር መሆኑ ተገልጹዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! 

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et  

Email;- aacaebc@gmail.com     

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

.

Copyright © All rights reserved.