Announcement የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤውን በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል አካሄደ።

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤውን በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል አካሄደ።

06th September, 2025

በጉባኤው የጽህፈት ቤቱ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ከመገምገሙ ባሻገር በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2017ዓ.ም የተመዘገበው የተማሪ ውጤት ትንተና ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ እና የመርሀግብሩ የክብር እንግዳ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ እየተመዘገበ ለሚገኘው ውጤት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው የጉባኤው ተሳታፊዎች የክፍለከተማውን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም በመገምገም በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪብሳ  በበኩላቸው ጉባኤው በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ የሚካሄድ እንደመሆኑ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በጉባኤው የሚቀመጡ የትኩረት መስኮችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መስተዋሉን የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኦል ሞሲሳ ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ ባካሄደው 32ኛ የትምህርት ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ጽህፈት ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ በ2017 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና የትምህርት ተቋማት ዕውቅና ተሰቷል።


.

Copyright © All rights reserved.