Announcement የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን” በሚል መሪ ሀሳብ አካሂዷል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን” በሚል መሪ ሀሳብ አካሂዷል፡፡

06th September, 2025

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናዖል ጫላን ጨምሮ የትምህርት አመራሮች፣ የዘርፉ ያሉ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተሸላሚ ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ በመክፈቻ ንግግራቸው መንግስት ኢትዮጵያን ታላቅና ገናና ለማድረግ በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ባለራዕይ ህዝብ እንዲፈጠር እየሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለአንድ አገር እድገት ትምህርት ወሳኝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲፀና፣ ልማትና ሁሉን አቀፍ ዕድገት እንዲመጣም የሚያስችል በመሆኑ ትምህርት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በክፍለ ከተማው ያሉ ባለድርሻ አካላት የትምህርት ዘርፍ ስራዎችን በማጠናከርና በማዘመን ሂደት ያላቸውን አስተዋፅኦ አጠናክረው በመቀጠል አገሪቱ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን በሚደረገው ርብርብ የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.