Announcement ብርሃን የዓይነስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

ብርሃን የዓይነስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

06th September, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብርሃን የዓይነ-ስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት  “ልዩ ፍላጎት ያላቸዉን የዓይነ-ስዉራን ተማሪዎች ዉጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ላይ ሁሉም ክልል የበኩሉን ሚና ይወጣ”  በሚል መሪ ሀሳብ ከክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮ ተወካይዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት  ጋር ዉይይት አካሄዳል፡፡

በብርሃን የዓይነ-ስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት  ዳይሬክተር ወይዘሮ ዉብአለም ደበበ የመወያያ ሰነዱን ባቀረቡት ወቅት ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራዉን ለማሳካት ብዙ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተራ  አክለዉም የትምህርት ቤቱን ራዕይና አላማን ለማሳካት የክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮዎች  ትብብር አስፋላጊ መሆኑንና ትምህርት ቤቱ የሀገር ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት በመጠቀም ሰብዓዊ ሀብት ግንባታ ላይ እንዲዉል ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ዉይይቱ የተሻለ ነገር ለማምጣትና ሁሉም በባለቤትነት ኃላፊነቱን እንዲወጠ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በተማሪ ምልመላ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራትና ግንዘቤን ማስጨበጥ እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበቸዉ አሳስበዋል፡፡

በቀጣይም ሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች ከትምህርት ቤቱ ጋር ስለተማሪዎች ወጤትና ስነምግባር እንዲሁም መማር ማስተማር ሂደት ዙርያ የሚወያዩበት መድረኮች እንደሚኖሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የጋራ ስራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.