Notice አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ የማስተዋወቅ ስራ መጀመሩ ተገለጸ።

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ የማስተዋወቅ ስራ መጀመሩ ተገለጸ።

02nd October, 2023

(መስከረም 19/2016 ዓ.ም) ስርዓተ ትምህርቱ ከመስከረም 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በሚቆየው መጽሀፉን የማስተዋወቅ መርሀ ግብር ከየትምህርት ቤቱ የተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራን፣የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሳነ መምህራን እና የ2ኛ ደረጃ ሱፐር ቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ በ2015 ዓ.ም በተመረጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ የነበሩ ግብአቶች ተካተው ዘንድሮ ወደ ሙሉ ትግበራ እንደመገባቱ ይዘቱን ለመምህራን እና ርዕሳነ መምህራን ማስተዋወቁ ከአተገባበር ጋር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ስለሚያቃልል ወደ ማስተቅዋወቅ ስራ መገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ገልጸው በመርሀ ግብሩ በ13 የትምህርት አይነቶች የተዘጋጁ የመጽሀፍ ይዘቶች እንደሚተዋወቁና ተሳታፊዎቹ በየክፍለ ከተማው ለቀሪ መምህራን በተመሳሳይ የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ በበኩላቸው መርሀ ግብሩ አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ አፍመፍቻ ቋንቋ ለሚማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጁ የመማሪያ በበኩላቸው መርሀ ግብሩ አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ አፍመፍቻ ቋንቋ ለሚማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጁ የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ የማስተዋወቅ ስራ የሚሰራበት መሆኑን ጠቁመው ስርአተ ትምህርቱ ዘንድሮ በሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደመደረጉ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮው ምክትል ኃላፊዎች እና አማካሪዎች ጋር በመሆን የመጽሀፍ ትውውቅ መርሀግብሩን በየክፍሉ ተገኝተው ተመልክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.