Notice የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ሙከራ አስጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ሙከራ አስጀመረ፡፡

14th September, 2023

(አዲስ አበባ 3/13/2015 ዓ.ም)   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስድስቱ ኢ- ስኩል ሶፍትዌሮች SMIS (SCHOOL MANAGEMENT INFORMATION SYSTEM) ውስጥ አንዱ ክፍል የሆነውን የተማሪዎች ምዝገባ ማካሄጃ ሶፍትዌር ሙከራ ማካሄድ ጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ የሶፍትዌሩን ሙከራ ትግበራ ለማካሄድ ከተመረጡ ሶስት ትምህርት ቤቶች አንዱ በሆነው ኮከበ ጽባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስጀምረዋል፡፡በሙከራ ትግበራውም ቀጣይ ተማሪዎች በራሳቸው ስምና የመግቢያ ኮድ (user name & password)መጠቀም  እንደሚስችላቸው ተነግሯል፡፡


በቀጣይ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የኦንላይን ምዝገባ በማካሄድ አሰራራቸውን ያዘምናሉ ያሉት የትምህርት ቴክኖሎጂ መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ  ሶፍት ዌሩን መጠቀም ተማሪዎች በራሳቸው ስምና የመግቢያ ኮድ በመጠቀም የሚሰጣቸውን አጋዥ ስራዎች ለመከታተልና የቤት ስራዎችን ለመስራት ያስችላቸዋል፤ እንዲሁም የዲጂታል ላይብረሪ ለመጠቀምና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡

ሶፍትዌሩ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ላይ ሲውል ቤተሰብ የልጁን ትምህር ሁኔታ በዲጂታል ዘዴዎች በመጠቀም መከታተል እንዲችሉና ትምህርት ቤቶችም በቂ የተማሪ መረጃ በተደራጀ መንገድ መያዝ የሚያስችል በዋናነትም የከተማዋን የትምህር መረጃ ችግር ሙሉ ለሙሉ የሚቀርፍ ይሆናል ተብሏል፡፡

የሙከራ ትግበራው እንደተጠናቀቀ በ2017 የትምህርት ዘመን ሶፍትዌሩ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የተለያ ደረጃዎችን በመከተልም ሌሎች የተሻሉ አገልግሎቶች መስጠት የሚችልበት ሂደት በቀጣይ ይዘረጋል ተብሏል፡፡

የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ርእሰ መምህር የሆኑት አቶ ዘውዴ ተሾመ በበኩላቸው ሲስተሙን በመጠቀም የተማሪዎች ምዝገባ በተቀላጠፈ መልኩ እየተካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


.

Copyright © All rights reserved.